በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

167

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

👉ባሕር ዳር ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ባሕር ዳር:መጋቢት 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

ከቀኑ 9 ሰዓት ኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ ከተማ ይጫወታሉ።

በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ ቡና በ22 ነጥብ 9ኛ እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ በ21 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ኢትዮጵያ ቡና ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች በአምስቱም አቻ ወጥቷል።

ተጋጣሚው ወልቂጤ ከተማ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ሁለት ጊዜ የተሸነፈ ሲሆን በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ አቻ ወጥቷል።

ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል።

በሌላኛው መርሐ-ግብር ባሕር ዳር ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ባሕር ዳር በ33 ነጥብ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ፋሲል ከነማ በ24 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ባሕር ዳር ከተማ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ዝቅ ያደርጋል።

የካቻምና የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ፋሲል ከነማ ጨዋታውን ካሸነፈ የአራተኝነት ደረጃን ከሐዋሳ ከተማ ይረከባል።

በተያያዘ ዜና ትናንት በተደረጉ 18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች አርባ ምንጭ ከተማ መቻልን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ የቅዱስ ጊዮርጊስና ሲዳማ ቡና ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck

Previous articleስፖርት ዜና ባሕር ዳር: ሚያዝያ 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ)
Next articleዋሊያዎቹ በሐምሌ ወር በአሜሪካ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።