
አዲስ አበባ: ሚያዝያ 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ)ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለታክስና ጉምሩክ ተገዥነት ለገቢ አሰባሰቡ ውጤታማነት ከሚዲያ ከፍተኛ መሪዎች ጋር በስካይ ላይት ሆቴል ዉይይት እያካሄደ ነው።
ወይዘሮ መሠረት መሥቀል የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ናቸው። መድረኩን ሲከፍቱ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን የጋራ መግባባት ለመፍጠር፤ መብትና ግዴታውን በውል የሚገነዘብ ዜጋ ለመፍጠር አይነተኛ መሳሪያ ነው።
ከሚዲያ መሪዎች ጋር ውይይት ማድረክ ያስፈለገውም ስለ ግብር አስፈላጊነት እና አሰባሰብ ለኅብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ነው ብለዋል።
ይሄም የራሷን መሠረታዊ ወጪ በራሷ ገቢ መሸፈን የምትችል ሀገር ለመፍጠር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ከአጋር አካላት ጋር በመሆን የንግድ እንቅስቃሴን በሚያውኩ፤ ግብርን በአግባቡ በማይከፍሉ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየወሰድን ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- በለጠ ታረቀኝ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!