
ባሕርዳር: መጋቢት 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ ኢፍጣር በኢትዮጵያ ሦስተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሐ-ግብር ነው በአዲስ አበባ የተካሄደው።
መርሐ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የዛሬው መርሐ-ግብር በጦርነት እና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን ድጋፍ የምናሰባስብበት በመሆኑ ደስታችንን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል ብለዋል።
ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ በበኩላቸው፣ በሀገር ደረጃ ለሦስተኛ ጊዜ የተካሄደው መርሐ-ግብሩ ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልጸው፣ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ አንድነቱን እና ሀገራዊ አብሮነቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚጠቅምም ተናግረዋል።
በመርሐ-ግብሩ ከተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የተወጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!