
ባሕር ዳር:መጋቢት 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ በሁርሶ ሰላም ማስከበር ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ የጉባ ኮርስ እና የድህረ ምረቃ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቁ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ በሁርሶ ማሰልጠኛ ያሰለጠናቸው እጩ መኮንኖች ዘመኑ የሚጠይቀውን ወታደራዊ ሳይንስ እና የአመራር ጥበብ የተካኑ መሆናቸው ተገልጿል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ጀነራል መኮንኖች፣ የቀድሞ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!