“የገቢ ስትራቴጅዎችን በማሳደግ የሕዝቡን የልማት ጥያቄ መመለስ ተገቢ ነው” የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀምበር

120

ባሕር ዳር:መጋቢት 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የገቢ ስትራቴጅ ዙሪያ ሀገር አቀፍ ዓውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።
በዓውደ ጥናቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ጌታቸው ጀንበር የገቢ ስትራቴጅን ማዘመን ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ እና የሕዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ያስችላል ብለዋል ። የክልላችን ገቢ እያደገ መጥቷል እንበል እንጅ ክልሉ በገቢ ራሱን ችሏል ማለት አይቻልም ነው ያሉት።
ሀገር አቀፍ ዓውደ ጥናቱ “ዘመናዊ የግብር አሥተዳደር ሥርዓት ቀጣይነት ላለው ልማት” በሚል መልዕክት ነው እየተካሄደ ያለው።
በዓውደ ጥናቱ ከፍተኛ የፌዴራል የመንግሥት ኀላፊዎች፣ የሁሉም ክልል የገቢዎች ቢሮ ኀላፊዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ባንኮች፣ የልማት ድርጅቶች፣ሲቪል ማኅበራት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- ትርንጎ ይፍሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበማኅበረሰቡ የሚነሱ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት እየሠራ እንደሚገኝ የገንዳውኃ ከተማ አሥተዳደር ገለጸ።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጉባ ኮርስ እና የድህረ ምረቃ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቁ ነው።