ለፖሊዮ ቅድመ መከላከል ዘመቻ የክትባት መድኃኒቶች እየሠራጩ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

170
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 27/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከሕዳር 12-15/2012 ዓ.ም ለሚካሄደው የፖሊዮ ቅድመ መከላከል ዘመቻ የክትባት መድኃኒቶችን እያሠራጨ መሆኑን የክትባት ፕሮግራም መድኃኒት ክትትል ባለሞያ ወይዘሪት ናዲያ ሲራጅ ገለጹ፡፡

የፖሊዮ ቅድመ መከላከል ዘመቻ በአገር አቀፍ ደረጃ በሕዳር ወር አጋማሽ እንደሚካሄድ ባለሙያዋ ገልፀው የክትባት መድኃኒቶቹን በኤጀንሲው 15 ቅርንጫፎች አማካኝነት ስርጭር እያካሄደ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
ክትባቱ ከ5 ዓመት በታች ላሉ 5 ሚሊዮን 373 ሺህ 171 ሕፃናት እንደሚሠጥ ገልፀው ኤጀንሲውም 5 ሚሊዮን 977 ሺህ 203 የክትባት መድኃኒቶችን እያሠራጨ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የክትባት መድኃኒቶቹ ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሆኑን አስታውቀው ኅብረተሠቡ ለክትባቱ ትኩረት ሠጥቶ ሕጻናትን ማስከተብ እንደሚገባውም ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ

Previous articleበሕግ የበላይነት ላይ ያተኮረ ውይይት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።
Next article“ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሲሠራ ሙስሊም፣ መስጅድ ሲሠራ ክርስቲያን የአሰሪ ኮሚቴ አባል የሚሆኑባት ሀገር ናት፡፡” የሃይማኖት አባቶች