ከ87 ሺህ በላይ የመማሪያ መጽሐፍት ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ድጋፍ ተደረገ።

57
ባሕርዳር: መጋቢት 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አይ አር ሲ የተባለ ድርጅት በአማራ ክልል በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች የሚውል የመማሪያ መጽሐፍትን ድጋፍ አድርጓል።
በአማር ክልል “አይ አር ሲ” የተባለ ድርጅት አስተባባሪ ሀብታሙ ሞላ እንዳሉት ድርጅታቸው በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት በደረሰባቸው 162 ትምህርት ቤቶች ላይ እየሠራ ይገኛል።
በዚህም በ24 ሚሊዮን ብር ወጪ ከ87 ሺህ በላይ መጽሐፍትን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት አሳትሞ ለቢሮው አስረክቧል። መጽሐፍቱ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል መማሪያ የሚያገለግሉ የአማርኛ፣ የእንግሊዝኛ፣ የሒሳብ፣ የአካባቢ ሳይንስ፣ ስፖርትና ሥነ ጥበብ የትምህርት አይነቶች ናቸው። ድርጅቱ በቀጣይ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ተምሕርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ወንደወሰን አቢ እንዳሉት የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት ችግር አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት እየፈተነው ይገኛል ነው ያሉት።
ችግሩን ለመፍታት 8 ነጥብ 8 ሚሊዮን የመማሪና ማስተማሪያ መጽሐፍት በውጭ ሀገር ቢታተሙም ወደ ሀገር ማስገባት የተቻለው 1 ነጥም 4 ሚሊዮን መጽሐፍት ብቻ ነው። አሁንም በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ሌሎች መጽሐፍትን ማስገባት አልተቻለም።
ከውጭ ታትመው ከተሰራጩት በተጨማሪ 900 ሺህ መጽሐፍት በሀገር ውስጥ ታትመው መሰራጨታቸውንም ነው ኀላፊው የገለጹት።
አሁን ላይ ትምህርቱ እየተሰጠ የሚገኘው በሶፍት ኮፒ መኾኑን ያነሱት ኀላፊው ሌሎች ድርጅቶችም በመጽሕፍ ሕትመቱ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊተሠራ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየፈተና ውጤት ማስታወቂያ
Next articleአዳዲስ የፈጠራ ውጤቶችን ወደ ተጠቃሚዎች በማድረስ የውጭ ምንዛሬ እጥረት መቀነስ እንደሚገባ የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ አስታወቀ፡፡