የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለ66 ፕሮጀክቶች ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ 34 ፕሮጀክቶችን ደግሞ ቦታ ነጠቀ፡፡

398

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 27/2012 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከባለ ሀብቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ እንደተገለጸው ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ 244 ፕሮጀክቶች ወደ ከተማዋ ገብተዋል፡፡ ከእነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ወደ ሥራ ባለመግባታቸው 5 ፕሮጀክቶች በፈቃዳቸው የወሰዱትን ቦታ መልሰዋል፤ ጽሕፈት ቤቱ የ34 ፕሮጀክቶችን ቦታ ሙሉ በሙሉ መንጠቁንም አስታውቋል፡፡ ሌሎች 34 ፕሮጀክቶች የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያና 32 ፕሮጀክቶች የመጨረሻ በድምሩ ለ66 ፕሮጀክቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ውይይቱ ባለሀብቶች ያሉባቸውን ችግሮች በመቅረፍ ወደ ሥራ እንዲገቡ እና ሌሎች ባለሀብቶችም በከተማዋ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈስሱ ለማስቻል የታሰበ ነው፡፡ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳድር ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ እንደገለጹት ደብረ ብርሃን ከተማ የአማራ ክልል ብቻ ሳትሆን የኢትዮጵያ ምሳሌ እንድትሆን እየተሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ይርጉ ፋንታ – ከደብረ ብርሃን
አዘጋጅ፡ -ዳግማዊ ተሰራ
ፎቶ፡- ሰሜን ሸዋ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት

Previous articleየኦክጅን እጥረቱ በመጠኑ መቃለሉን አብመድ ያነጋገራቸው በክልሉ የሚገኙ የጤና ተቋማት ገለጹ፡፡
Next articleበሕግ የበላይነት ላይ ያተኮረ ውይይት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።