አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት መድኃኒት በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ሆስፒታሎች ድጋፍ ተደረገ፡፡

81
ደሴ:መጋቢት 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አንድ ሚሊዮን ብር የሚያወጡና የተለያዩ ህመሞችን ለማከም የሚያገለግሉ መድኃኒቶችን በወሎ ዩኒቨርሲቲ በኩል ጉዳት ለደረሰባቸው ሆስፒታሎች እንዲከፋፈሉ ማስረከባቸውን የግሎኬር ፋርማ ማኑፋክቸሪንግ ተወካይ ኃላፊ ናሊኒ ናያክ ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም በገበያ ውስጥ በቀላሉ የማይገኙ መድኃኒቶችን ድጋፍ ለማድረግ እንሠራለን ነው ያሉት።
ድጋፉ በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ደሴ ሪፈራል እና ቆቦ ሆስፒታሎች እንደሚከፋፈል የገለጹት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየለ (ዶ.ር) ድጋፉ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ወኪል እንዲመጣ ላስተባበሩት የልማትና ደቨሎፕመንት ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ ሳንዶካን ደበበን አመስግነዋል።
የልማትና ደቨሎፕመንት ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ እና የወሎ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል ሳንዶካን ደበበ በበኩላቸው ግሎኬር ፋርማ መድኃኒት አምራች ድርጅት ያደረገው ድጋፍ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሆስፒታሎች ያለባቸውን የመድኃኒት እጥረት ለማቃለል የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ሌሎች ረጂ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ በጋራ አንሠራለን ብለዋል።
ዘጋቢ፡- አሊ ይመር
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleግንባታው የዘገየውን የገበዘ ማርያም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማጠናቀቅ እንደሚሠራ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡
Next articleየጤና ትምህርት ጥራትን ይበልጥ ለማሻሻል የሚያስችል ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ተካሄደ።