
ባሕርዳር፡- መጋቢት 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ቸልሲን ከሊቨርፑል ያገናኘው ተጠባቂው ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡
በፕሪሚዬር ሊጉ ደካማ የውድድር ጊዜን እያሳለፉ የሚገኙት ሁለቱ ክለቦች የተገኛኙበት ጨዋታ ግብ አልታየበትም፡፡ በውጤት ቀውስ የሚገኘው ቸልሲ አሰልጣኙን ካሰናበተ በኋላ ያደረገው የመጀመሪያው ጨዋታው ነው፡፡ ከአሰልጣኙ መሰናበት በኋላም ግብ ማስቆጠር ተስኖት አምሽቷል፡፡
በማንችስተር ሲቲ ከተሸነፈ በኋላ ወደ ስታፎርድብሪጅ ተጉዞ ሌላኛውን ታላቅ ጨዋታ ያደረገው ሊቨርፑልም ወደ ድል መመለስ አቅቶታል፡፡
አሰልጣኙን ያሰናበው ሌስስተር ሲቲ በሜዳውና በደጋፊው ፊት በአስቶንቪላ ተሸንፏል፡፡ እንግዳው ክለብ አስቶን ቪላ 2 ለ 1 አሸንፎ ተመልሷል፡፡ በሌላ ጨዋታ ሊዲስ ዩናይትድ ከመመራት ተነስቶ ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ1 አሸንፏል፡፡ በርንማውዝ በሜዳውና በደጋፊው ፊት በብራይትን 2 ለ0 ተሸንፏል፡፡
በታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!