በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ ይጫወታል፡፡

420
ባሕርዳር፡- መጋቢት 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ ከብሬንትፎርድ ጋር ይጫዋታል፡፡
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ ከብሬንትፎርድ የሚያገኛው ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ ነጥብ እየጣለ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ ምሽት አራት ሰዓት ላይ በሜዳው ይጫወታል፡፡
ማንችስተር ዪናይትድ ካለፉት ሦስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መካከል በሁለቱ ተሸንፏል፡፡
በአንደኛው ደግሞ አቻ ወጥቷል፡፡
ጨዋታው ምሽት 4፡00 በኦልድትራፎርድ ይደረጋል፡፡
ማንችስተር ዩናይትድ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ ያደርጋል፡፡
በሌለ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ዌስትሃምና ኒውካስትል ይገናኛሉ፡፡
ጨዋታው በተመሳሳይ ምሽት 4፡00 ይደረጋል፡፡
ኒውካስትል ዩናይትድ በዛሬው ጨዋታ ድል ከቀናው ሦስተኛ ደረጃውን ያስጠብቃል፡፡
ነጥብ የሚጥል ከሆነና ማንችስተር ዩናይትድ የሚያሸንፍ ከሆነ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃውን በዩናይትድ ይነጠቃል፡፡
በታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበስፔን የንጉሥ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና ከ ሪያል ማድሪድ ጋር ይጫወታል፡፡
Next articleተጠባቂው ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡