በስፔን የንጉሥ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና ከ ሪያል ማድሪድ ጋር ይጫወታል፡፡

165
ባሕርዳር፡- መጋቢት 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያንን ትኩረት በመሳብ የሚታወቀው ኤልክላሲኮ ዛሬ ምሽት ይደረጋል፡፡
በስፔን ላሊጋ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ በስፔን የንጉሥ ዋንጫ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ይገናኛሉ፡፡
ከእግር ኳስ ጨዋታ በላይ የክብር ጉዳይ የሚነሳበት የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ሁልጊዜም ትኩረት ይስባል፡፡
በቀድሞ ኮከቡ ዣቪ እየተመራ ያለው ባርሴሎና ላሊጋውን በሰፊ የነጥብ ልዩነት እየመራ ነው፡፡
በአውሮፓ መድረኮች ግን በጊዜ ተሰናብቷል፡፡
ለፍጻሜ ለማለፍ የሚደረው ውድድር ብርቱ ፉክክር እንደሚደረግበት ይጠበቃል፡፡
ጨዋታው ምሽት 4፡00 በካምፕኑ ይደረጋል፡፡
በታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበኢትዮጵያ ዳርት ሻምፒዮና አማራ ክልል ሁለተኛ በመውጣት አጠናቀቀ፡፡
Next articleበእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ ይጫወታል፡፡