በኢትዮጵያ ዳርት ሻምፒዮና አማራ ክልል ሁለተኛ በመውጣት አጠናቀቀ፡፡

108
ባሕርዳር፡- መጋቢት 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ከመጋቢት 20-23/2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲካሄድ የቆየው 17ኛው የኢትዮጵያ ዳርት ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቋል፡፡
በአጠቃላይ በውድድሩ በሁለቱም ፆታዎች በታዳጊና በአዋቂ በነጠላ፣ በጥንድ፣ በድብልቅ (በወንድና በሴት) እና በቡድን በተደረገ ውድድር ፡
1ኛ አዲስ አበባ 456
2ኛ አማራ 337
3ኛ ደቡብ 319
4ኛ ሐረሪ 279
5ኛ ሲዳማ 217
6ኛ ድሬደዋ 127
7ኛ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 12 ነጥብ በመያዝ ውድድራቸውን በማጠናቀቅ የሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በውድድሩ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተጫዋቾች የማጣሪያ ውድድር በማድረግ መስከረም ላይ ለሚካሄደው የዓለም የዳርት ሻምፒዮና ላይ በቀጥታ ሀገራቸውን በመወከል ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡
በውድድሩ ላይ የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቢልልኝ መቆያ፣ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሳ ተበጀ እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ አባላትና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article12 ቢሊዮን ብር ያካበቱ ባለሃብቶች ወደ ቡሬ የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ገብተዋል።
Next articleበስፔን የንጉሥ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና ከ ሪያል ማድሪድ ጋር ይጫወታል፡፡