በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያየ።

95
ባሕር ዳር:መጋቢት 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ጋር ተወያይቷል፡፡
በአቶ አደም ፋራህ የተመራ እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋን ያካተተው የኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ ልዑካን ቡድን በሶማሊያ የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡
የልዑካን ቡድኑ በቆይታቸው ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ልዑኩ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከን መልዕክት ለሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ማድረሱም ተጠቁሟል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የእያንዳንዱ ዜጋ የምግብ ፍላጎት መረጋገጥ አለበት” የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ሴቶች ሊግ
Next article12 ቢሊዮን ብር ያካበቱ ባለሃብቶች ወደ ቡሬ የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ገብተዋል።