አቶ ደመቀ መኮንን በተመድ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ጋር ተወያዩ።

113
ባሕር ዳር:መጋቢት 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ እርዳታ አሥተባባሪ ካትሪን ሶዚ ጋር ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም አቶ ደመቀ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች እና መንግሥት ከተመድ እና ኤጄንሲዎቹ ጋር የሚያደርገውን ትብብር ለማጠናከር ያለውን ፍላጎት አስረድተዋል።
ከሰላም ስምምነቱ ጋር በተያያዘ በሰጡት ማብራሪያም መንግሥት ብሄራዊ ምክክር፣ የሽግግር ፍትሕ፣ ብሄራዊ ዕርቅ እና በተጎዱ አካባቢዎች የተሃድሶ እና የመልሶ ግንባታ ለማካሄድ ያለውን ቁርጠኝነት በተመለከተ ገለጻ አድርገውላቸዋል።
አቶ ደመቀ አያይዘውም ለጋሽ እና የተመድ ኤጄንሲዎች መንግሥት እያደረገ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ካትሪን ሶዚ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በፕሪቶሪያ ለደረሰው የሰላም ስምምነት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበኩር ጋዜጣ በመጋቢት 25/2015 ዓ/ም ዕትም
Next articleከቻግኒ-ድባጤ የአስፋልት መንገድ በቀጣይ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ፡፡