“የኢትዮ – አንጎላን ግንኙነት ማጠናከር ይገባል” አቶ ደመቀ መኮንን

91
ባሕር ዳር:መጋቢት 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ለበርካታ ዓመታት የዘለቀውን የኢትዮ-አንጎላ ወዳጅነት በቢዝነስ ዘርፉም ማጠናከር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡
አቶ ደመቀ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የአንጎላ አምባሳደር ፉራንሲስክ ጆስ ዲክሩዝን አሰናብተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት እንዲጠናከር አምባሳደሩ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኢትዮ- አንጎላ ግንኙነት ከተለመደው ፖለቲካ ባሻገር በቢዝነስና እና ኢቨስትመንት የማደግ ዕድል እንዳለው አቶ ደመቀ አስረድተዋል፡፡
አምባሳደር ፉራንሲስክ ጆስ ዲክሩዝ የኢትዮጵያ ባለሀብቶች በአንጎላ ለመሰማራት ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleለመጪዎቹ በዓላት ከ13 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለገበያ ይቀርባል።
Next articleመጋቢት 15/2015 ዓ.ስ ኽምጠ ዊከ ጋዜጠ