ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።

281
ባሕር ዳር: መጋቢት 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛው መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶችን በአዲስ ተሿሚዎች ተክቷል።
በዚህ መሰረትም ምክር ቤቱ የወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ኾነው እንዲሾሙ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ወይዘሮ ዘሃራ ኡመርን ደግሞ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ኾነው እንዲያገለግሉ ምክር ቤቱ አጽድቋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየተጀመሩ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ተቋሙ የክትትልና ድጋፍ ሥራ እያከናወነ ይገኛል።
Next articleለመጪዎቹ በዓላት ከ13 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለገበያ ይቀርባል።