የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ።

113
ባሕርዳር : መጋቢት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ)በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ-ግብር የሦስተኛ ቀን ውሎ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ኢትዮጵያ መድን ከአርባ ምንጭ ከተማ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በደረጃ ሰንጠረዡ ኢትዮጵያ መድን በ30 ነጥብ 3ኛ እንዲሁም አርባ ምንጭ ከተማ በ18 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በሌላኛው የሊጉ መርሐ-ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ድሬዳዋ በ21 ነጥብ 11ኛ ደረጃን የያዘ ሲሆን በአንጻሩ ለገጣፎ ለገዳዲ በስድስት ነጥብ የመጨረሻው 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በተያያዘም ትናንት በተደረጉ 17ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌትሪክን 2 ለ 0 እንዲሁም ፋሲል ከነማ ወላይታ ዲቻን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ-ግብር ነገ ወልቂጤ ከተማ ከባሕር ዳር ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየጊቤ ሁለት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የጥገና ሥራዎች እየተከናወኑለት ነው።
Next articleየጠቅላይ ሚኒስትሩ የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ጉብኝት