የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት የጦር ጀነራሎች መኮንኖች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።

215
ባሕር ዳር:መጋቢት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦር አመራር መኮንኖች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
ቡድኑ የኢንስቲትዩቱን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጅ መሰረተ ልማት ዓቅም እና እየተከናወኑ ያሉ የምርምር እና ልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ኢንስቲትዩቱ እያከናወናቸው ባሉ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው የጎሉ የምርምር እና ልማት ሥራዎች ዙሪያ ለቡድኑ አባላት ገለጻ አድርገዋል።
የኤርትራ የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦሩ አመራሮች ቡድን አስተባባሪ ጀነራል አብርሃ ካሳ በኢንስቲትዩቱ ያደረጉት ጉብኝት ለሀገራቸው ብዙ ልምድ የቀሰሙበት መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በቴክኖሎጂው ዘርፍም አብረው መስራት የሚያስችላቸው ዕድል ስለመኖሩም የተገነዘቡበት ጉብኝት መሆኑን መናገራቸውን ከኢንስቲትዩቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየጊቤ ሁለት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የጥገና ሥራዎች እየተከናወኑለት ነው።
Next articleየውሻ እብደት በሽታን በማስከተብ መከላከል እንደሚገባ የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።