
ባሕርዳር: መጋቢት 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አትሌት አበጀ አያና በዛሬው ዕለት በተካሄደው የፓሪስ ማራቶን ድል ቀንቶታል።
አትሌቱ ውድድሩን ያሸነፈው 2 ሰዓት 07 ደቂቃ ከ14 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ነው።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጉዬ አዶላ 2 ሰዓት 07 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ውድድሩን በሁለተኛነት ሲያጠናቅቅ፣ ኬንያዊው አትሌት ጆስፋት ቦይት ደግሞ ሦስተኛ ሆኖ ጨርሷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!