
ባሕር ዳር: መጋቢት 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የወፍላ፣ ኮረምና ዛታ ነዋሪዎች ማንነታቸው እንዲከበር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
“በሰልፉ ማንነታችን አይቀየርም፤ እኛ ዋግሹሞች እንጂ ትግራይ አይደለንም፤ ማንነታችን ይከበር በማለታቸው በትግራይ ኃይሎች የታሰሩ ወገኖቻችን ይፈቱ” የሚሉ መልእክቶችን በሰላማዊ ሰልፉ እያሰሙ ነው።
ሰሎሞን ደሴ – ከኮረም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!