
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መከላከያ ሚኒስቴር በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ለደቡብ ዕዝ የሰራውን የጦር መምሪያ የሻለቃ መኖሪያና መሥሪያ ካምፕ በዛሬው እለት አስመርቋል።
በምረቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ጀነራል መኮንኖች፣ የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘመናዊ ካምፑ የኮር ጠቅላይ መምሪያና የሬጅመንት ጠቅላይ ሠፈር በርካታ ዘመናዊ አገልግሎት የሚሰጡ ግንባታዎች ያካተተ መሆኑን የግንባታው ፕሮጀክት ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ዳኛቸው ያዴታ ለኢዜአ ገልጸዋል።
ካምፑ የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ ሆስፒታልና የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ እንዲሁም የመሰብሰቢያ፣ የመመገቢያ አዳራሾችና የመዝናኛ ማዕከላት መያዙን ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!