የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በዋና ዋና ተልዕኮዎቹ እና አፈጻጸማቸው ዙሪያ በባሕር ዳር ከተማ ምክክር እያደረገ ነው።

200
ባሕር ዳር :መጋቢት 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በዋና ዋና ተልዕኮዎቹ እና አፈጻጸማቸው ዙሪያ በባሕር ዳር ከተማ ምክክር እያደረገ ነው።
በውይይቱ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀንበር (ዶ.ር)፣ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያ እና የተባበሩት መንግሥታት ተወካይ ሚስተር ኬሊዮፓስ ቶሮሬ ተገኝተዋል።
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በጦርነት የወደሙ ተቋማትን መልሶ ስለመገንባት እና የቀድሞ ተዋጊዎችን ለማቋቋም ድጋፍ በሚደረግበት አግባብ ዙሪያ ነው ውይይት የሚያደርገው።
ኮሚሽኑ ማኅበረሰብን ትኩረት ያደረገ መልሶ ማቋቋም እንዲደረግ እና ሀገራዊ ዘላቂ ሰላም፣ ማኅበራዊ ትስስር፣ ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚ፣እንዲሁም ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን እንዲፋጠን በትኩረት እንደሚሠራ ተጠቁሟል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና ብሔራዊ ባንክ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ዝውውር ተዋናዮችን በጥናት በመለየት ቀጣይ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታወቁ።
Next articleበርሃማነትን ተከላካይ ዘቦች