የሽግግር ፍትሕ በተለያየ ጊዜ ለተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ፍትህ የሚገኝበት ፣ ተጎጂዎች ሁለንተናዊ ፈውስ የሚያገኙበትና ስለተፈጸሙ ነገሮች እውነቱ የሚነገርበት መኾኑ ተገለጸ።

55
አዲስ አበባ፡ መጋቢት 21/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤትና የደህንነት ጥናቶች ተቋም በጋራ በሽግግር ፍትሕ ላይ ያተኮረ የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ጥናት አካሂደዋል።
አውደ ጥናቱ ከሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ቀረፃ እስከ ትግበራ ባለው ሂደት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያግዝ ውይይት እንዲደረግበት ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡
የአውደ ጥናቱ አላማ በሽግግር ፍትሕ ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ የመንግስትና መንግስታዊ ያልኾኑ አካላት በሽግግር ፍትሕ ዙርያ ሊኖራቸው ስለሚገባው ሚና ተቀራራቢ ግንዛቤ እንዲኖር ማስቻል መኾኑን የኢትዮጵያ ሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዲቨሎፕመንት ዳይሬክተር ወይዘሮ ሀና ወልደ ገብርኤል ተናግረዋል፡፡
በአውደ ጥናቱ ላይ ሁሉንም ክልሎች ጨምሮ ከአዲስአበባና ድሬዳዋ የመጡ የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ፣የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተወካዮች እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡- ሳሙኤል ኪሮስ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleፍኖተ ጋፋት – ተሸላሚው የልዩ ባለተሰጥኦዎች ማዕከል
Next articleኻምል 15/2014 ዓ.ስ ኽምጠ ዊከ ጋዜጠ