
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመንገድ ግንባታዎችን በተመለከተ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሀገሪቱ 320 የመንገድ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ መንገዶችን ለማጠናቀቅ 1 ትሪሊየን ብር እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ በኢትዮጵያ እስካሁን ከተጠናቀቁ መንገዶች ብልጫ እንደሚኖራቸውም ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ ከ22 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ እየተገነባ መኾኑንም አስረድተዋል፡፡
በመንገድ ግንባታ እየተሠራ ያለው ሥራ አበረታች መኾኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአብነት በባሕር ዳር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የድልድይ ግንባታ በበጀትም ኾነ በጥራቱ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ አለመሠራቱን አንስተዋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች የተጀመረውን የመንገድ ግንባታ የሚያጓትቱ ምክንያቶች መኖራቸውንም ገልጸዋል፡፡
በበጀት፣በዲዛይን፣ በግንባታ እቃዎች ዋጋ መጨመር ፣በጨረታ ሂደት እና በተያያዥ ምክንያቶች የመንገዶች ግንባታ እንዳይጓተት መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በፋሲካ ዘለዓለም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!