“ገበታ ለሸገር እና ገበታ ለሀገር በቅርቡ ወደ ገበታ ለትውልድ ያድጋሉ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

454
ባሕር ዳር: መጋቢት 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ11ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ በእንደራሴዎቹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል የቱሪዝም ልማት ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡
ጠቅለይ ሚኒስትሩ ጥንታዊ ታሪክ፣ ማራኪ መልካ ምድር እና ቱባ ባሕል ያላትን ኢትዮጵያ የቱሪዝም ማዕከል ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡ ለቱሪዝም እንቅስቃሴ ችግሩ መሠረተ ልማት እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት አለመሟላታቸው ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሩን ለመፍታት እየተሠራ መኾኑን አንስተዋል፡፡
አዲስ አበባን ለማስዋብ ገበታ ለሸገር የተለየ ለውጥ እንዳመጣ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ገበታ ለሀገር አድጎ ጎርጎራ፣ ኮይሻ፣ ወንጪ እና አላላ ኬላ በቅርቡ እንደሚጠናቀቁ ገልጸዋል፡፡ ጎርጎራ በቀጣዮቹ አራት ወራት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚኾንም ጠቁመዋል፡፡
“ገበታ ለሸገር እና ገበታ ለሀገር በቅርቡ ወደ ገበታ ለትውልድ ያድጋሉ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ሶማሊያ ስድስት የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ግንባታ ይጀምራሉ ብለዋል፡፡ በግል የሚሠሩ ሁለት ፕሮጀክቶች አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ሚዛን ቴፒ ለመገንባት ዲዛይናቸው ተጠናቀዋል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
Next articleየበጋ መስኖ ስንዴ በወፋላ ወረዳ እና ኮረም ከተማ