የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ነው።

101

ባሕር ዳር: መጋቢት 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።
የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው።
እስካሁንም ከኦነግ ሸኔ፣ ከሰላምና ጸጥታ፣ ከሰላም ስምምነት፣ ከዜጎች መፈናቀልና ግድያ፣ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ዜጎች፣ የሱዳን ወታደሮች ወረው የያዙትን የኢትዮጵያ መሬትና ያወደሟቸውን ንብረቶች፣ የኑሮ ውድነት፣ የመሠረተልማትን የተመለከቱ ጥያቄዎች ቀርበዋል።
አሁንም የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ናቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የኢትዮጵያ ረቂቅ ሙዚቃዎች እናት” እማሆይ ጽጌማርያም ገብሩ በ100 ዓመታቸው አረፉ።
Next article“የብሔር ፖለቲካ እና የዘር አሰላለፍ ለአሁናዊ የሀገሪቱ ችግሮች መንስኤ እየሆኑ መጥተዋል” የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት