በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምናና ትምሕርት ክፍል ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ጥገና አገልግሎት መጀመሩን ገለጸ።

120
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምናና ትምሕርት ክፍል ፋይት ብላይንድነስ ኢን ኢትዮጵያ ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ጥገና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
የቀዶ ሕክምና አገልግሎቱም በሞራ ግርዶሽ ምክኒያት ለማየት የተቸገሩ ታካሚዎችን እይታ ለመመልስ ያለመ ነው።
ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ጥገና አገልግሎቱ እስከ መጋቢት 22/2015 ዓ.ም ችግሩ ያለባችሁ ሰዎች ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን ሕክምና ክፍል በመገኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መኾን እንደሚቻል ሆስፒታሉ ጥሪ አቅርቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleስፖርት ዜና ባሕር ዳር: መጋቢት 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ)
Next articleየሀገር በቀል ዕውቆቶች ፋይዳ