
ባሕር ዳር :መጋቢት 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት የመንግሥትን የስድስት ወር አፈጻጸም ሪፖርት ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ፡፡
ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚቀርበውን ሪፖርት ያዳምጣል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ የተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!