ኢትዮጵያ እና ቻይና በግብርናው ዘርፍ በትብብር ለመስራት የተፈራረሙትን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ወደ ትግበራ ለማስገባት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገለጹ።

76
ባሕር ዳር :መጋቢት 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ቻይና በግብርናው ዘርፍ በትብብር ለመስራት የተፈራረሙትን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ወደ ትግበራ ለማስገባት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይና የግብርና ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር ክፍል ዳይሬክተር ኒ ሆንግሺንግ እንዲሁም በሚኒስቴሩ የዓለም አቀፍ ትብብር ክፍል የምዕራብ እስያና አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሊዩ ጂያንግ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያና ቻይና በግብርናው መስክ በትብብር ለመስራት የፈረሙትን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሊተገበሩ ወደሚችሉ ፕሮጀክቶች በመቀየር ተጨባጭ ውጤት እንዲመጣ ጠንካራ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ሁለቱ ወገኖች በግብርና ጉዳዮች ያላቸውን ትብብር አስመልክቶ መደበኛ የሆነ የምክክር ጊዜ ለማዘጋጀት ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያና ቻይና በግንቦት 2014በግብርና፣ኢንዱስትሪ፣ ፋርማሲዩቲካል፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ መሰረተ ልማትና ጤና መስኮች በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የኢንቨስትመንት ስምምነቶች መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleከመራጩ ኅብረተሰብ በተነሱ ጉዳዩች ላይ ከአስፈፃሚ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።
Next article“የሰላም እና የፀጥታ ችግሮች እንዲሁም የኑሮ ውድነት መሠረታዊ የሕዝብ ጥያቄዎች ሆነዋል”