
ባሕር ዳር :መጋቢት 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከመራጩ ኅብረተሰብ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ከአስፈፃሚ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።
ምክር ቤቱ በዓመት ሁለት ጊዜ ከመረጠው ሕዝብ ጋር ውይይት የሚያደርግ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህም በየካቲት ወር ባደረገው የሕዝብ ውክልና ሥራ ከመራጩ ሕዝብ ጋር በተደረገ ውይይት የተነሱ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የሠላም እና የኑሮ ውድነትን የተመለከቱ ጥያቄዎች ለሚመለከተው አስፈፃሚ አካላት መቅረቡ ተገልጿል።
የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ መሠረት ኃይሌ በየምርጫ ክልሉ የነበረው የውይይት ሂደትን በተመለከተ ሪፖርት አቅርበው ውይይት እየተደረገ መሆኑን ከምክር ቤቱ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!