“በጦርነት ማግስት የቆቦ ከተማ አርሶ አደሮችን በመደገፍ በዚህ ልክ ማልማት በመቻሉ የሚደነቅ ነው” ኀይለማርያም ከፍያለው (ዶ.ር)

92
ወልድያ፡ መጋቢት 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ኀይለማርያም ከፍያለው (ዶ.ር) በሰሜን ወሎ ዞን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን እየጎበኙ ነው።
ጉብኝቱ በቆቦ ከተማ አሥተዳደር በአርሶ አደሮች ማሳ የለማን 67 ሄክታር የስንዴ ማሳ በመቃኘት ነው የተጀመረው፡፡
ከተማ አሥተዳደሩ በጦርነት ማግስት አርሶ አደሮችን በመደገፍ በዚህ ልክ ማልማት በመቻሉ መደነቃቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ ኀላፊ ሀይለማርያም ከፍያለው (ዶ.ር) ተናግረዋል።
የንጋት መስኖ ማኀበር ሰብሳቢ አርሶ አደር በሪሁን ውዱ የስንዴ አዝመራ ለአካባቢው አዲስ በመኾኑ ለመቀበል ተቸግረው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የግብርና ባለሙያዎች ባደረጉት ሙያዊ ድጋፍ እና ክትትል መሰረት በመዝራታቸው ጥሩ ውጤት እንዳዩበት ተናግረዋል፡፡ ወደፊት ተጨማሪ ማሳ ለማልማት ማቀዳቸውንም ተናግረዋል።
በሰሜን ወሎ ዞን 14 ሺህ 52 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ተሸፍኗል።
ዘጋቢ፦ካሳሁን ኃ/ሚካኤል
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“በቀጣይ እንደመሪ ፓርቲ ነፃነትን በአግባቡ መጠቀምና ማስተዳደር ላይ መስራት ይገባል” አቶ አደም ፋራህ
Next articleየጤና መድኅን አገልግሎቱን የተሻለ ለማድረግ አባላቱ በቂ የአባልነት መዋጮ መክፈል እንደሚገባቸው የምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ገለጸ።