በቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ አሸናፊ ሆነች።

213
ባሕር ዳር:መጋቢት 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር በአትሌቶች መካከል የተካሄደውን ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፣ ፅጌ ገብረ ሰላማ ሁለተኛ እንዲሁም መልክናት ውዱ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሰዋል።
የዘንድሮው ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄደው ይህ ሩጫ መነሻ እና መድረሻውን አዲስ አበባ ቦሌ አትላስ አካባቢ አድርጎ እየተካሄደ ነው ።
በውድድሩ የሴቶችና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ ሻለቃ አትሌት ኋይሌ ገብረ ሥላሴ፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ አትሌት ለተሰንበት ግደይን ጨምሮ የተለያዩ አትሌቶችና እንግዶች ተገኝተዋል።
የ2015 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎሜትር ሩጫ ”ቦታዬ፤ መብቴ፤ ድምፄ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው በዚህ ውድድር አትሌቶች፣ 15 ሺህ የጤና ሯጮች፤ እንዲሁም አምባሳደሮች እየተሳተፉ ነው።
በአትሌቶች መካከል በሚደረገው ፉክክር ለአንደኛ ደረጃ 70 ሺህ ብር፣ ለሁለተኛ ደረጃ 45 ሺህ ብር እንዲሁም ለሦስተኛ ደረጃ 30 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበጾም ወቅት የተራበን በማብላት ፣ በመተዛዘንና በመደጋገፍ የፈጣሪን ትዕዛዝ መፈጸም እንደሚገባ የሐይማኖት አባቶች ተናገሩ።
Next articleየሃይማኖት አባቶች በሰላም ግንባታ