
ወልድያ፡ መጋቢት 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ዩኒቨርሲቲው በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካሰለጠናቸው ተማሪዎች በተጨማሪ በልዩ ልዩ የትምህርት ዘርፎች በድህረ ምረቃ 112 ሰልጣኞችን አስመርቋል።
ዩኒቨርስቲው ከቅዱስ ላሊበላ ቅርስና ጥናት ግቢ 25 ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በድህረ ምረቃ መርሀ ግብር አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት 160 ሴት አና 430 ወንድ በድምሩ 592 ተማሪዎችን አስመርቋል።
የዩኒቨርሲቲው ኘሬዝዳንት አበበ ግርማ ( ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው በወልድያ፣ በመርሳና በላሊበላ ግቢዎች በጤና፣ በቱሪዝም፣ በግብርናና በቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከላት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከ2004 ዓ ·ም ጀምሮ የምርምርና የልህቀት ሥራ እየሠራ ይገኛል።
ዘጋቢ፦ ካሳሁን ኃይለሚካኤል
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!