“የሀገረ መንግሥቱን ኅልውና አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ የሰላም ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ በስፋት እየተስተዋሉ መጥተዋል” የሠላም ሚኒስትር አማካሪ አምባሳደር እሸቱ ደሴ

60
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሠላም ሚኒስቴር ከአማራ ክልል ሠላም እና ጸጥታ ቢሮ ጋር በጋራ “የሃይማኖት አስተምህሮ ለሠላም” በሚል መሪ ሃሳብ የሠላም ምክክር በባሕር ዳር እያካሄደ ነው።
ውይይቱን የከፈቱት የሠላም ሚኒስትሩ አማካሪ አምባሳደር እሸቱ ደሴ፤ የሀገረ መንግሥቱን ኅልውና አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ የሰላም ችግሮች ከጊዜ ጊዜ በስፋት እየተስተዋሉ መጥተዋል ብለዋል። ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታት ውይይት እና ምክክር አስፈላጊ ነው ያሉት አማካሪው፤ የዚህ ምክክር ዓላማም ችግሮችን እና ምክንያቶቻቸውን ነቅሶ በማውጣት ዘላቂ መፍትሄ ማፈላለግ ነው ብለዋል።
ሃይማኖትን መሰረት አድርገው የሚፈጠሩ ችግሮች ሦስት መሰረታዊ መነሻዎች አሏቸው ያሉት አምባሳደር እሸቱ ችግሮቹም በሃይማኖት ተቋማት የሚፈጠሩ ውስጣዊ ችግሮች፣ በተለያዩ የሃይማኖት ተቋማ መካከል የሚስተዋሉ ቁርሾዎች እና በሃይማኖት ተቋማት እና በየደረጃው ባለው የመንግሥት አስፈጻሚ አካል መካከል የሚፈጠሩ ልዩነቶች ናቸው ብለዋል። የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ ድርሻዎችን መውሰድ ከምክክሩ የሚጠበቅ ነው ብለዋል።
በምክክሩ ከሠላም ሚኒስቴር፣ ከክልል የጸጥታ ተቋማት፣ ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የተውጣጡ አባቶች፣ ምሁራን እና የሀገር ሽማግሌዎች ተሳታፊዎች ናቸው።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ከአማራ ሕዝብ አንድነት ውጪ የሚፈቱ አይደሉም” የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መልካሙ ተሾመ
Next article“አረጋውያን አባቶች ሀገራቸውን ጠብቀው ሲያቆዩ የተጠቀሙበትን ጥበብ ለትውልድ ሊያስተላልፉ ይገባል” የአማራ ክልል አረጋውያን ማኅበር