
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎጃም፣ ባሕር ዳር ከተማና አዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር አመራሮች “ድሎችን የማፅናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ የአመራር ተልዕኮ” በሚል መሪ መልዕክት በፍኖተ ሰላም ከተማ ውይይት እያካሄዱ ነው።
በመድረኩ ላይ የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ፤ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች የሚመለሱት አንድነታችን የጠነከረ እንደኾነ ብቻ ነው ብለዋል። የዚህ ወቅት አመራር ትውልዱንና የትግል አውዱን የሚመጠን መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል።
አቶ መልካሙ ፖለቲካ የግለሰብ ውድድር ሳይሆን የቡድን ጉልበት የሚፈልግ በመኾኑ መንገዳችን ይህንን የተከተለ መኾን ይገባዋል ማለታቸውን ከምዕራብ ጎጃም ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!