ከሁለት ሚሊዮን በላይ የኀብረተሰብ ክፍሎችን በአማራጭ የኃይል ምንጭ ተጠቃሚ ማድረጉን የአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ፡፡

89
ደሴ :መጋቢት 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን ሶስት ወረዳዎች የተገነቡ የባዮጋዝ የኃይል አማራጮች በባለ ድርሻ አካላት ተጎብኝተዋል፡፡
በአማራ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል የማያገኙ የኀብረተሰብ ክፍሎችን አማራጭ የኃይል ምንጭ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ነው።
በደቡብ ወሎ ዞን ጃማ፣ወረኢሉና ለገሂዳ ወረዳዎች የተገነቡ የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂዎች የክልልና የደቡብ ወሎ ዞን የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ማኀበረሰብ በተገኙበት ተመርቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያም በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የኀብረተሰብ ክፍሎችን የአማራጭ የኃይል ምንጭ ተጠቃሚ ለማድረግ ከ3000 በላይ ባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂዎችን አስገንብቷል፡፡ በዚህም 13 ሺህ 567 ቤተሰቦች የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ መኾናቸውን የደቡብ ወሎ ዞን ውኃና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ጽጌ ተናግረዋል።
በክልሉ ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚኾኑ በገጠር የሚኖሩ የኀብረተሰብ ክፍሎችን አማራጭ የኃይል ምንጭ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጥላሁን ሽመልስ ተናግረዋል። በደቡብ ወሎ ዞን ሶስት ወረዳዎች የተገነቡትና አገልግሎት መስጠት የጀመሩት የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጅዎች የዚሁ ዕቅድ አካል መኾናቸውንም አቶ ጥላሁን ጠቁመዋል። በቀጣይ ተጨማሪ አርሶ አደሮች የአማራጭ የኃይል ምንጭ ተጠቃሚ እንዲኾኑ ይሠራልም ብለዋል።
የወረኢሉ እና ለገሂዳ ወረዳ አርሶ አደሮች እንዳሉት የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጅ ተጠቃሚ በመኾናቸው ጊዜና ጉልበታቸውን በአግባቡ ለመጠቀም አግዟቸዋል፡፡ ከባዮ ጋዝ በሚገኘው ብርሃንም ልጆቻቸው ጤናቸው ተጠብቆ ማንበብ በመቻላቸው በትምህርታቸው ውጤታማ እየኾኑ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡- አሊ ይመር
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።
Next articleኢትዮጵያ ከረመዷን ጾም እዝነትን፤ ከሁዳዴ ጾም ምኅረትን አብዝታ ትጠብቃለች፡፡