ዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

68
ባሕር ዳር :መጋቢት 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ አስታወቁ።
የዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ጉብኝት አሰመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ የተለያዩ የልማት ጉዳዮች ላይ የጋራ ትብብርን ማጠናከር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ጉብኝቱ ኢትዮጵያ ዓለም ባንክ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር ነው ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቷ፣ በኢትዮጵያ ለልማት አመቺ የሆኑ ተግባራትን መመልከታቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው ኢፕድ ነው።
የኢትዮጵያ በርካታ ፈተናዎችን በመቋቋም እየወሰደች ያለውን አኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችንም አበረታተዋል።
በተለይም የኮቪድ 19፣ የሰሜኑ ግጭት፣ ድርቅ እንዲሁም የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በኢኮኖሚው ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተጽእኖ በቀላሉ እንደማይታይ ጠቁመው፣ የኢኮኖሚ ተጽእኖዎችን ለመቋቋም በምታደርገው ሂደት ዓለም ባንክ ድጋፍ እንደሚያድርግ ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ከ391 ሚሊዮን ብር በላይ በሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ስምምነት ተፈጸመ።
Next articleከሁለት ሚሊዮን በላይ የኀብረተሰብ ክፍሎችን በአማራጭ የኃይል ምንጭ ተጠቃሚ ማድረጉን የአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ፡፡