“ሀገሩን የሚወድ፣ ብቁና አምራች ዜጋ ለማፍራት የአመጋገብ ሥርዓትን ማዘመን ወሳኝ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

93
ባሕር ዳር:መጋቢት 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገሩን የሚወድ፣ ብቁና አምራች ዜጋ ለማፍራት የአመጋገብ ሥርዓትን ማዘመን ወሳኝ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በምግብና ስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ ዳሰሳ ጥናት ይፋ ማድረጊያ መርኃ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም የመንግሥት አጀንዳ ዜጋ ተኮር በተለይ ለደሀ ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።
ዛሬ ይፋ የተደረገው ሀገር አቀፍ የዳሰሳ ጥናት የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽነትን ለማስፋት ወደ ተሟላ እንቅስቃሴ ለመግባት የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።
በምግብና ሥርዓተ-ምግብ ስትራቴጂ የዜጎችን የተሟላ አመጋገብ ሥርዓት ማረጋገጥ ለነገ የማይባል ነው ያሉት አቶ ደመቀ የተመጣጠነ ምግብ ማሟላት የቅንጦት አጀንዳ አይደለም ነው ያሉት።
በኢትዮጵያ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ስትራቴጂን ለመተግበር ግጭትን በማስቆም ዘላቂ ሰላምን ማፅናትና የኑሮ ውድነትን መከላከል ይገባልም ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ መንግስት ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠርና በመከላከል ሰላም ለማስፈንና የኑሮ ውድነትን ለማርገብ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ድርቅና የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በኑሮ ውድነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን ገልጸው፣ ምርትን በመደበቅ የኑሮ ውድነቱን በሚያባብሱ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
“ሀገሩን የሚወድ፣ አምራችና ብቁ ዜጋ ለማፍራት ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓት ወሳኝ በመሆኑ ምርታማነትን ማሻሻል ቀጣይ ስራችን ነው” ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“በአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ላይ በተሠራው ሥራ ክልሉ የተረጋጋ እንዲኾን ማድረግ ተችሏል”የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሰላኝ ጣሰው
Next articleየአለም አቀፍ የሸማቾች ቀን