
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 24/2012 ዓ.ም (አብመድ) የስዊድን የጤና እና የማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ሌና ሀሌንገር የሚመራ ልዑክ ዛሬ በጤና ሚኒስቴር በመገኘት ጉብኝት አድርጓል::
ከልዑካን ቡድኑ ጋር የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት እንዲሁም በዘርፉ በትብብር የሚሠሩ ሥራዎች ላይ ውይይት እንዳደረጉ የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር አሚር አማን (ዶክተር) ተናግረዋል፡፡
ዶክተር አሚር የልዑካን ቡድኑ ላደረገው ጉብኝት በራሳቸውና በመሥሪያ ቤታቸው ስም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
ሁለቱ አገራት በጤና ዘርፍ በአጋርነት ብዙ ሥራዎችን እንደሚሠሩ ሙሉ እምነት እንዳላቸውም ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል፡፡