ዋሊያዎቹ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቀኑ::

185
ባሕርዳር: መጋቢት 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቀና፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በኮትዲቯር አስተናጋጅነት በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ከጊኒ ብሔራዊ ቡድን ጋር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን መጋቢት 15 እና 18 ቀን 2015 ዓ.ም በሞሮኮ ያደርጋል።
የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ከመጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ልምምዳቸውን ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ዋልያዎቹ ከትናንት በስቲያ ከሩዋንዳ አቻቸው ጋር ባደረጉት የአቋም መለኪያ ጨዋታ በከነዓን ማርክነህ ግብ 1 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወቃል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አራት ከግብጽ፣ ከማላዊና ከጊኒ ጋር ተደልድሏል፡፡
እስከአሁን ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎችም በሦስት ነጥብ እና በአንድ የግብ ክፍያ ምድቡን እየመራ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየ3ኛው ዙር የባሕር ዳር ማረሚያ ቤት የሕግ ታራሚዎች የስፖርት ውድድር ተጀመረ፡
Next article“የረመዷን ፆም ዛሬ ጨረቃ ከታየች ነገ፣ ካልሆነ ግን ከነገ በስቲያ ይጀምራል” የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት