የሰላም እሴቶችን ለመገንባት የሴቶች ሚና የላቀ መሆኑ ተጠቆመ።

49
ባሕር ዳር:መጋቢት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ “በሚል በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲከበር የቆየው ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን የንቅናቄ ማጠቃለያ መርሐ ግብር በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ላለፉት ወራት በተከናወኑ የማኅብረሰብ አቀፍ ንቅናቄ ሥራዎች ሴቶችን ከተጠቂነት መከላከል መቻሉን ገልጸዋል።
ሀገራችን ላለፋት ጊዜያት ያጋጠማት ሰው ሰራሸ ችግሮችን ለመታደግ የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ባሕላችንን ለማስቀጠል የምንሰራበት ጊዜ ነውም ብለዋል።
የተለያዩ የፓናል ውይይቶችን በማካሄድና በሰላም ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር ፣ በየደረጃው ያሉ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች መሰራታቸውንም ነው የገለጹት፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በሴቶች ጉዳይ ሲሰራ መቆየቱንም ሚኒስትሯ አስታውሰዋል፡፡
በአፋር ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላሰተር አስተባባሪ አሚና ሴኮ በበኩላቸው ፥ የሰላም እሴቶችን ለመገንባት የሴቶች ሚና የላቀ መሆኑን አብራርተዋል።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ የሠላም ሚኒስትር ዲኤታ ታዬ ደንደአን ጨምሮ ከተለያዩ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ምርታማነትን ስናስብ ጤናማ ዜጎችን ማፍራት ዋናው ትኩረታችን ሊሆን ይገባል” የደቡብ ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ
Next articleወጣቶች የኢትዮጵያዊያን መጻኢ ዕጣ ፋንታ የተሳሰረ እና የማይለያይ መኾኑን በውል መገንዘብ እንዳለባቸው የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አዳም ፋራህ ተናገሩ።