በጎንደር ከተማ የተካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ ተጠናቅቋል፡፡

152

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 23/2012 ዓ.ም (አብመድ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር በማይልኮ ሎጂ አዘጋጅነት የተካሄደው ሕዝባዊ ሩጫ በሠላም ተጠናቅቋል፡፡ ለቅዱስ ሩፋኤል የዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት ድጋፍ ለማሰባሰብ ዓለማ ያደረገው የጎዳና ላይ ሩጫ በርካቶች ተሳትፈውበታል፡፡

የውጭ ዜጎችን ጨምሮ ከ1 ሺህ 800 ያላነሱ ተሳታፊዎች በ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫው ተሳትፈዋል፡፡ ዓይነ ስውራን ተማሪዎችም ‹‹እኛን ለማገዝ ስለሮጣችሁ እናመሠግናለን›› ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- እመቤት ሁነኛው -ከጎንደር

Previous articleድርቁን ተከትሎ ሊከሰት የሚችል በሽታን ለመከላከል የተቀናጀ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ፡፡
Next article‹‹የመማፀኛ ከተማ›› የተሰኘ መጽሐፍ ጎንደር ላይ እየተመረቀ ነው፡፡