የአማራ ባንክ መርሀባ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን መጋቢት 9 በይፋ የሚመረቅ መኾኑን ገለጸ።

366
አዲስ አበባ: መጋቢት 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ባንክ መርሀባ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን መጋቢት 9 በይፋ የሚመረቅ መኾኑን ገልጿል።
ባንኩ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት በተለያዩ የአገልግሎት አማራጮች ለደንበኞቹ ቅርብ በመኾን ላይ መኾኑን ተገልጿል ።
በአፍሪካ መሪ እና ጨዋታ ቀያሪ እንዲሁም ተወዳዳሪ የመኾን አላማን አንግቦ መነሳቱን ባንኩ ገልጿል።
እስካሁን በተጓዘባቸው መንገዶች ከፍተኛ የካፒታል አቅምን በማጎልበት ተወዳዳሪ ለመኾን የሚያስችል ቁመና በመገንባት ላይ ሲሆን ተወዳዳሪ ለመኾንና አላማውን ለማሳካት ቀልጣፋ፣ በሁሉም ተደራሽ ፣ ጊዜውን ያማከለ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ተብሏል።
በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን በባንክ ወለድ ምክንያት ከባንክ የራቁ ደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት በወለድ ከሚሰጡት መደበኛ የባንክ አገልግሎት በኅብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት በማግኘቱ በከፍተኛ ኹኔታ በማስፋት እና በማደግ ላይ እንደሚግርኝ ባንኩ ገልጿል ።
May be an image of 13 people and indoor
ባንኩ በአሁኑ ጊዜ በሁሉም የመደበኛ የባንክ አገልግሎት በሚሰጡ ከ230 ቅርንጫፎች በላይ በመስኮት በኩል የተሟላ የመርሀባ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት በመስጠት ላይ መገኘቱን ባንኩ አመላክቷል።
እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ 30 ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችን ለመክፈት በዝግጅት ላይ መኾኑን ባንኩ ገልጿል።
አማራ ባንክ ልማቱን ለማቅረብ የሚያስችለውን ተቋም በመለየት በዘርፉ የታወቀ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ተመርጦ የሥራ ስምምነት ውል በማድረግ የፕሮጀክት ሥራውን ማስጀመሩ ተመላክቷል።
አማራ ባንክ ለመርሀባ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከመደበኛው ሲስተም ጎን ለጎን ከወለድ ነፃ ቋት ራሱን ችሎ በካምፓኒ ደረጃ በመለየት የኮር ባንኪንግ ሲስተም መተግበሩን ተጠቅሷል።
ባንኩ በቅርቡም ከወለድ ነፃ የዲጂታል ማይክሮ ብድር እና ፋይናንስ አገልገሎት ለማቅረብ ዝግጅት ያጠናቀቀ መኾኑን ባንኩ ገልጿል።
በመጨረሻም መጪው የረመዳን ወርን እርስ በርስ በመተጋገዝና በጎ ተግባራትን በመፈጸም የምናሳልፍበት እንዲኾን እመኛለሁ ብሏል ።
ዘጋቢ:- አየለ መስፍን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleአሚኮ ስፖርት ዜና
Next articleኢትዮጵያና ሱዳን በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፎች በትብብር ለመሥራት ተስማሙ።