በፕሪሚየር ሊጉ ባሕር ዳር ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 1 አሸነፈ።

107
ባሕርዳር:የካቲት 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሕር ዳር ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 1 አሸነፈ፡፡
በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው የ16ኛ ሳምንት መርኃ ግብር የጣና ሞገዶቹ ከመመራት ተነስተው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተከታታይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሶስት ነጥብ አስመዝግበዋል፡፡
ለባሕር ዳር ከነማ ሀብታሙ ታደሰ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ፉአድ ፈረጃ ቀሪዋን አንድ ጎል አስቆጥሯል፡፡
የኢትዮ ኤሌክትሪክን ብቸኛ ጎል አብነት ደምሴ በ51ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ ነጥባቸውን ወደ 30 ከፍ በማድረግ ከኢትዮጵያ መድን ጋር እኩል ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል፡፡
የ16ኛ ሳምንት መርኃ ግብሮች ሲቀጥሉ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከነማ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleʺየሚጣሩ አንደበቶች፣ አጉራሽ ያጡ ጉሮሮዎች”
Next articleየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን ረቡዕ ይጀምራል።