ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ.ብሊንከን ጋር ተወያዩ።

109

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አሕመድ ዛሬ ረፋድ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ.ብሊንከን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በተለያዩ የሀገር ውስጥ፣ ቀጣናዊ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ተስማምተዋል።
ኢትዮጵያ በሰላም ስምምነቱ ላይ እያስመዘገበች ያለችው ስኬት ተቀባይነት አግኝቷል። በኢኮኖሚው፣ በልማት ጥረቶች፣ በተለይም በግብርና እና በቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ያሉ ጉዳዮችም ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል። መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በኅልውና ዘመቻው ትክክለኛውን የሙያ ሥነ ምግባርና ተግባር በእናንተ ውስጥ አይተናልና ልትመሰገኑ ይገባል” የጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ
Next articleየቅጥር ማስታወቂያ