
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ የንጉስ ተክለሃይማኖት ቤተ መንግሥት አካል የኾነና ለረዥም ጊዜ ታጥሮ የነበረን ቦታ ለማልማት የእድሳት ሥራ መጀመሩን የከተማ አሥተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው ኀላፊ አቶ መንግሥት ጅጋር እንደገለፁት፤ ከተማ አሥተዳደሩ የንጉስ ተክለሃይማኖትን ቤተ መንግሥት በማደስ የቱሪስት መዳረሻ እንዲኾንና የአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲጎበኘው ለማድረግ ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መንገድ ለመሥራት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የቤተ መንግሥቱ አንድ አካል የኾነው ከአደባባዩ በስተጀርባ ለረዥም ጊዜ ታጥሮ የነበረውን ቦታ ለማልማት ከ5ሚሊየን ብር በላይ በመመደብ በይፋ ሥራ መጀመሩን የገለፁት አቶ መንግሥት የማልማት ሥራውንም መንቆረር ኮንስትራክሽን እየሠራ ነው ብለዋል።
የሚለማው ቦታ መልካምድር አቀማመጡ አስቸጋሪ በመኾኑ በጥራት እንዲሠራ መምሪያቸው አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አቶ መንግሥት ጅጋር መናገራቸውን የከተማ አሥተዳደሩ መንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!