
በተወሰኑ አካባቢዎች የተገነቡ የመስኖ ፕሮጀክቶች ሥራ ተጀምረዋል።
የመስኖ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ በመግባታቸው በአማራ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ በበጋ ወቅት ብቻ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሄክታር መሬት በመስኖ ማልማት ተችሏል፡፡ ለዚህ ውጤት መገኘት የመስኖ ፕሮጀክቶች ሥራ መጀመር በመቻላቸው ነው፡፡
ክልላችን የከርሰ ምድርና ገጸ-ምድር ውኃ ባለጸጋ ነው። ጸጋውን አልምቶ መጠቀም ደግሞ ያልተቋረጠ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል። አርሶ አደሩ በስፋት ዘመናዊ የውኃ መሳቢያ ፓምፕ መጠቀም በመቻሉ በግብርና ሥራው ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ችሏል፡፡ በቀጣይም ትላልቅ ወንዞች ባሉበት የክልላችን አካባቢ የመስኖ ግድቦችን እንሠራለን፡፡
በአማራ ክልል በቂ ምርት አለ፤ ምርት እንደሌለ በማስመሰል የኢኮኖሚ አሻጥር በሚሠሩና ያለ አግባብ ምርት በሚሰበስቡ ነጋዴዎን እና ደላላዎች ላይ መንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ ይህን ማድረግ ስንችል እየታየ ያለውን ሰው ሠራሽ የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት መመለስ እንችላለን፡፡

አርሶ አደሩ ሳይበለጽግ ኢትዮጵያ በለጸገች ማለት አይቻልም፡፡ በአጠቃላይ የሀገርን ልማት ለማፋጠን
አርሶ አደሩ ላይ ትኩረት አድርገን መሥራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
ዶክተር ይልቃል ከፋለ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር
መረጃው የርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈትቤት ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!