
ባሕርዳር: መጋቢት 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበረው የ2ተኛው ምዕራፍ ሁለተኛ ዙር የልማታዊ ሴፍቲኔት የማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
መርሐ ግብሩ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 56 ከተሞችና በ1ሺ 40 ቀበሌዎች የሚተገበር መኾኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
መርሐ ግብሩ በከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ 227 ሺህ 932 ዜጎቸን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ። ከእነዚህ ተጠቃሚዎች መካከል 43 ሺህ የሚኾኑ ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንደሚኾኑም ተገልጿል፡፡
መርሐ ግብሩ ከ2015 እስከ 2017 ዓ.ም የቆይታ ጊዜ ሲኖረው በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄድ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ መስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የፌዴራልና የክልል ከተሞች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችን ጨምሮ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!