“ወጣቶች ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና መሠረት መኾን አለባቸው” ዶክተር ጋሻው አወቀ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ።

158
ባሕር ዳር:መጋቢት 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና በባሕር ዳር ከተማ ተጀምሯ።
በሥልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ዶክተር ጋሻው አወቀ እንዳሉት በወጣቱ አቅም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማሳካት የሚጠይቅ ወቅታዊ ኹኔታ ላይ ነው የምንገኘው። ሥልጠናው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክር፣ከዚህ ቀደሙ የተለየ ውጤትንም የምንጠብቅበት ነው ብለዋል።
በሥልጠናው ወጣቱ የብልጽግና እሳቤዎችን እንዲያውቅ የሚያስችል ፣ለሁለንተናዊ ግንዛቤም የሚያግዝ መሠረት የሚጣልበት ነው ብለዋል።
በሀገራዊ እና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ሀገርን ለማሻገር የወጣቶች ሚና ላይ ያተኮሩ ሥልጠናዎች ይሰጣሉ ነው ያሉት።
May be an image of 1 person
“ኢትዮጵያ ፈተናም፤ በረከትም ያለባት ሀገር ናት፣ በሰከነ እና በቀናነት በመነጋገር ችግሮችን መፍታት፣ለሰላምና እድገት መትጋት ያስፈልገናል ያሉት ደግሞ የብልጽግና ጽሕፈት ቤት የወጣቶች ሊግ ፕሬዚዳንት አቶ አክሊሉ ታደሰ ናቸው።
ወጣቶች በሰፈር የታጠረ፣ኢትዮጵያዊነትን የማይመጥን አስተሳሰብ ተሸካሚ መኾን የለባቸውም፣ለዚህም ተከታታይ የአስተሳሰብ ግንባታና የአቅም ማጠናከሪያ ሥራዎች ይሠራሉ ብለዋል። የሊጉን መዋቅር የማስተካከል ሥራም እየተከናወነ መኾኑን ተናግረዋል።
ለወጣቶች የተዘጋጀው ስልጠና ለሰላም ፣ለልማትና ሀገራዊ መግባባት ትርጉም ያለው እንደኾነ የተናገሩት አቶ አክሊሉ ስልጠናው በታለመለት ዓላማ ልክ እንዲፈጸምም አደራ ብለዋል።
ለቀጣይ 8 ቀናት የሚቆየው ስልጠናው “በወጣቶች አቅም የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ይረጋገጣል” የሚል መሪ መልዕክት አለው።
ዘጋቢ:-ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዓመታዊ ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ገቡ።